ለሊሴ ነሜ በአግዋ ተጠቃሚነት ጉዳይ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሺር ለሊሴ ነሜ ከአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ የንግድ ባለሙያ ያሱኢ ፓይ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ የአግዋ ተጠቃሚነቷን እንድትቀጥል የአሜሪካ ኤምባሲ ከኮሚሽኑ ጋር በቅንጅት በመስራት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
አሜሪካ ከግንቦት 1992 ጀምሮ ለአዳጊ አገራት ከሰጠችው የቀረጥ ነፃ ንግድ ማበረታቻ መርሃ ግብር (አግዋ) ኢትዮጵያን ለማቀብ ፍላጎት ማሳየቷ ከኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!