መስከረም 4/2015 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለመከላከያ ሰራዊት ከ118 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
በመርኃ ግብሩ ላይ የተቋማቱ አመራሮች ድጋፉን ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ አስረክበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና በስሩ ያሉ 18 ተጠሪ ተቋማት ከ90.8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 361 የቁም ከብቶችን በማቅረብ ደጀንነቱን ያሳየ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ 26 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በበኩሉ ወደ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ሶስቱም ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት በአጠቃላይ ከ118 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ በዛሬው አድርገዋል።
በደረሰ አማረ