ለመከላከያ ሰራዊት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ እና የ30 ሰንጋ ድጋፍ ተደረገ

ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ) አገርን ለማስቀጠል በሚደረገው ርብርብ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ለተሰለፈውና ድል እያስመዘገበ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

በዚህ መሰረትም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የ15 ሚሊዮን ብር እንዲሁም የ30 ሰንጋ ድጋፍ አድርጓል።

በተመሳሳይም አማዝ ኤሌክትሮኒክስ ማኑፋክቸሪንግ 250 ሺሕ ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ኅብር ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ብር እንዲሁም ሌሎችም ግለሰቦች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የጠላት ኃይልን በማጀገን የኢትዮጵያን መፃኢ እጣ ፈንታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ለመክተት እየሰሩ ያሉ አካላትን ፍላጎት ለማምከን እንዲሁም የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ሰንኮፍ የሆነውን አሸባሪው ሕወሓት ግብአተ መሬት ለማቃረብ የሚደረጉ ቁሳዊ እና የሞራል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ተብሏል።

በሄብሮን ዋልታው