ለሠራዊቱ ደም እንለግስ – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) –ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሠራዊቱ ደም እንለግስ፤ የዐቅመ ደካሞችን ቤት እናድስ፤ አረንጓዴ ዐሻራችንን እናሳርፍ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የግብርና ምርታማነታችንን በእጥፍ እናሳድግ ሲሉም ነው በማህበራዊ ትስር ገጻቸው ያሰፈሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የየቢሮ ሥራችንን ዐቅምና ጊዜ ጨምረን እንሥራ፤ እያንዳንዳችን ከሚጠበቅብን በላይ ስንወጣ፣ ሁሉም ነገር ይስተካከላል” ነው ያሉት፡፡