ለረጅም ጊዜ የኦነግ ሊቀመንበር የነበሩት ኦቦ ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) ለረጅም ጊዜ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት ኦቦ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው “ኦሮሚያ ጠንካራ ሰው አጥታለች” ብለዋል።

“ገላሣ ዲልቦ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ነበሩ” ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ሙሉ ህይወታቸውን ለኦሮሞ ሕዝብ የገበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀዘን መግለጫቸው ለኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ ብርታትን እመኛለሁ ብለዋል።

ኦቦ ገላሳ ዲልቦ የ1983 ሽግግር ወቅትን ጨምሮ ለረጅም ጊዜ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡