ለተፈናቃዮች የደቡብ ክልል የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ

መስከረም 2/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለኅልውና ዘመቻው 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ከተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ምግብና ቁሳቁስ ተበርክቷል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው አሸባሪው ሕወሓት የከፈተው ጦርነት የአማራ ክልል እዳ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊያንን ኅልውና የመታደግ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ያደረግነው እና በቀጣይም የምናደርገው ድጋፍ ችሮታ ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል።

ጦርነቱ በመላው ኢትዮጵያዊያን ላይ የተከፈተ መሆኑን ገልፀው ኢትዮጵያ ዳግም ወደቀደመ ክብሯ ትመለሳለች ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡