ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የደንና የመሬት ገጽታ ማገገሚያ መርኃግብር ይፋ ሆነ

ታኅሣሥ 19/2014 (ዋልታ) የግብርና ሚኒስቴር፣ ዓለም ዐቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢኒስቲትዩትና ኮሪያ ዓለም ዐቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በጋራ የሚተገብሩት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የደንና የመሬት ገጽታ ማገገሚያ መርኃግብር ይፋ ሆነ።
በተመረጡ የተፋሰስ አካባቢዎች የተራቆተ መሬት መልሶ እንዲያገግም የማድረግ ዓላማ ያለው መርኃግብሩ የማስፈጸሚያ 9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለታል።
 
ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ይህ መርኃግብር የማስፈጸሚያ ወጪውን የሚሸፍነው የኮሪያ ዓለም ዐቀፍ የትብብር ኤጀንሲ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
 
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!