ለአገር መከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው

ታኅሣሥ 11/2014 (ዋልታ) የተለያዩ ተቋማት ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ለሰራዊቱ ድጋፍ ያደረጉት የሰቪል ሰርቪስ ኮሚሸን፣ የኦሮሚያ ክልል ሀብት አሰባሰብ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጉራጌ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና እና የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ናቸው።

የሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለአገር መከላከያ ሰራዊት 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ሲያደረግ ለተፈናቀሉ ወገኖችም ከ400 ሺሕ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኦሮሚያ ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ በበኩሉ ከ3 ዞኖች ከ26 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ የዓይነት ድጋፍ ማድረጉ ተመላክቷል።

ክልሉ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ373 ሚሊየን ብር በላይ ደጋፍ ማድረጉም ተጠቅሷል።

በሚኪያስ ምትኩ