ለአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ወደ ጎንደር ሽኝት እየተደረገ ነው

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) በጎንደር ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ለሚደረገው የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ (ቁንዳላ)የሽኝት መርሃግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ከብሔራዊ ሙዚየም ተነስቶ ወደ 4 ኪሎ አደባባይ ሽኝቱ እየተደረገ ሲሆን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ አባት አርበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
መቅደላ ላይ ከእንግሊዝ ጋር ሲዋጉ እጅ አልሰጥም ብለው በጀግንነት ራሳቸውን ለአገራቸው መስዋዕት ያደረጉት አፄ ቴዎድሮስ ሹርባቸው ለ150 አገር በውጭ አገር እጅ መኖሩና ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ መደረጉ ይታወሳል።