“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል የጎዳና ላይ ውድድር በወልቂጤ ተካሄደ

ሰኔ 19/2014 (ዋልታ) “ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል የ15 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ውድድር በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።

ኬሮድ ኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ ነው የተካሄደው።

ውድድሩ ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር ለመስበክ ታሳቢ ያደረገና ሁሉንም ማኅበረሰብ ያሳተፈ ውድድር እንደሆነ ተገልጿል።

ውድድሩን በሴቶች ሶፊያ አሰፋ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ መሰረት ዓለማየሁ እና አበራሽ ሺልማ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው ገብተዋል።

በወንዶች ውድድር ድንቅዓለም አየለ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አብራራው ምስጋናው እና ሌሊሳ አራርሳ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ ችለዋል።

ሚኪያስ ምትኩ (ከወልቂጤ)