”ለኢትዮጵያ እንቁም” የተሰኘ ዘመቻ በለንደን ተካሄደ

”ለኢትዮጵያ እንቁም” የተሰኘ ዘመቻ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) በለንደን በተከበረው 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ የጥቁር ሕዝቦች በሆነው የኢትዮጵያ የዓለም ፌዴሬሽን በተሰኘ ድርጅት አዘጋጅነት “ለኢትዮጵያ እንቁም” የተሰኘ ዘመቻ ተካሂዷል።

በመርሃግብሩ በእንግሊዝ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለስ የተገኙ ሲሆን ላዘጋጁት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ የዓድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዊያን ነጻነትም የላቀ ሥፍራ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በዓድዋ ድል በዓል የመታሰቢያ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን የሚወክሉ ቡድኖች፣ ድርጅቶች እና በዩናይትድ ኪንግደም የራስ ተፈሪያን ንቅናቄ አባላት መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW