ለጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እየተካሄደ ነው


ሐምሌ 11/2013(ዋልታ) –
ለጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ሀገር አቀፍ የእውቅናና ምስጋና መረሃ-ግብር በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡
መረሃ-ግብሩ በዋናነት በተለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዛሬ የተጀመረው አገር አቀፍ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ኢዜአ ዘግቧል።