ኅዳር 5/2015 (ዋልታ) ሕንዳዊው ቢሊየነር ሙከሽ አምበኒ የእግሊዙን ዝነኛ ክለብ ሊቨርፑልን ለመግዛት ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን አስታወቁ፡፡
ቱጃሩ ሙከሽ አምበኒ የመርሲሳይዱን ክለብ ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን ረብጣ ዶላር በመመደብ ክለቡን የራሳቸው ለማድረግ እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡
የክለቡ ባለቤት ፈንዌይ ስፖርት ግሩፕ ክለቡን ለመሸጥ የወሰነ ሲሆን ለክለቡ ሽያጭም አራት ቢሊዮን ፓውንድ ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡
ሙከሽ አምበኒ አጠቃላይ ሀብታቸው 94 ቢሊዮን ዶላር ሲተመን በፎርብስ መፅሔት ዝርዝር ላይ በስምተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የዓለማችን ቢሊየነር ናቸው፡፡
የ65 ዓመቱ ህንዳዊ ሙከሽ አምበኒ በነዳጅ፣ ቴሌኮም እና ሌሌች የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ባለሃብት መሆናቸውን ዘሰን ዘግቧል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW