ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪይ ይሰጣሉ

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ኅዳር 5/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ነገ ኅዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አመላክቷል።

በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ አስታውቋል።