ሕወሓት የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም

ኅዳር 4/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ሙከራ በአፋር ልጆች ተጋድሎ ቅዠት ሆኖ ቀርቶበታል ሲሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።

በአፋር ክልል የፈንቲረሱ ዞን ወጣቶች በፈጠሩት ጠንካራ አደረጃጀት የሽብር ቡድኑን ታጣቂዎች መግቢያ መውጫ አሳጥቷቸዋል ነው የተባለው።

የአካባቢው ወጣቶች ኢትዮጵያዊነትን ከአፋር ልብ ፍቆ ማውጣት ባይችልም የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ግን በ27 ዓመት የአገዛዝ ዘመኑ አፋርን በአገሩ ባይተዋር አድርጎት ቆይቷል ብለዋል።