መምሪያው በሥራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላት እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር እያካሄደ ነው

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) የመከላከያ ኅብረት ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ በሥራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላቱ የእውቅናና የምስጋና መርሃግብር እያካሄደ ነው፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የዋና መምሪያው በስሩ ለሚገኙ ኮሌጆችና አካዳሚዎች በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላሳዩና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላት የሜዳይና የማዕረግ ዕድገት እንደሚሰጥ ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡