መሪያችን ከቤተ መንግስት ወጥቶ እኛ እቤት አንቀመጥም – የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) መሪያችን ከቤተ መንግስት ወጥቶ እኛ እቤት አንቀመጥም ሲሉ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ፈለግን በመከተል በቁርጠኝነት ወደ ግምባር ዘመቱ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገር ለማዳን ወደ ግምባር መዝመቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቀፎው እንደተነካ ንብ ከዳር እስከዳር ተነቃንቋል።

ለሽብርተኞች ቦታ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ሲሉ ወደ ግምባር እየዘመቱ ሲሆን ለመዝመት ለተዘጋጁ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችም ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ለሀገራቸው የሚዘምቱት ሀገር ወዳድ ወጣቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሂክማ ኬሬዲን እንዲሁም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ቆንጂት ደበላ በድል ተመለሱ ሲሉ ጀግኖቹን ሸኝተዋል።

ክፍለ ከተማው በተጨማሪም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በዓይነት በአጠቃላይ 31 ሚሊዮን 165 ሺሕ ብር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

ጉለሌ ክፍለ ከተማ እስካሁን ለመከላከያ ሰራዊት ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉም ነው የተገለፀው።

 

በሀኒ አበበ