የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ  ላይ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው በፃፉት መልዕክት መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም፤ በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን ሲሉም አክለዋል።