መንግሥት ለበጎ ፈቃድ ዘማች ተማሪዎች ምስጋና አቀረበ

ታኅሣሥ 2/2014 (ዋልታ) የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ላይ ለሰነበቱ ተማሪዎች መንግሥት ምስጋና አቀረበ፡፡

የተማሪዎች የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ተጠናክሮ መሰንበቱን ያስታወሰው መንግሥት መርሃ ግብሩ ተማሪዎች ኢትዮያዊነትን ያስመሰከሩበት መሆኑን ገልጿል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ተማሪዎች የአርሶ አደሮችን ሰብል መሰብሰብን ጨምሮ በተለያዩ በጎ ፈቃዶች ላይ እንዲሰማሩ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ መሰንበቱን በመጥቀሰ ነው ለዚህም መንግሥት ምስጋና ያቀርባል ያሉት፡፡

በአገር ዐቀፍ ደረጃ ሁሉም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ1 ሳምንት ተዘግተው ተማሪዎች በበጎ አድራጎት ሥራ መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡

ተማሪዎቹ የተሰጣቸውን የ1 ሳምንት አገራዊ አበርክቷቸውን በመጨረሳቸው ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡