መንግሥት ከኢትዮጵያ ጎን የሚቆሙ በርካታ አገራትና ማኅበረሰብ ተገኝቷል አለ


ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) መንግሥት ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ላይ ከሚደረገው ጫና በላይ ብዙ ለአገሪቱ የቆሙ አገራትና ማኅበረሰብ አግኝተናል አለ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ እየሰጡ ባለው መግለጫ ኢትዮጵያ ዳግም የነፃነት አርማ ሆናለች በርካታ የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያን በመከተል ለነፃነታቸው እየታገሉ ነው ብለዋል፡፡

በሳምንቱ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል አግኝተናል ነው ያሉት፡፡

ዲያስፖራው አገሪቱን ለመደገፍ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ይፋ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ የእርዳታና ድጋፍ ሥራ እየሰራ ነው፡፡