መንግሥት ያሉንን ትሩፋቶች ካሉብን ተግዳሮቶች በማስበለጥ መጓዝ እንደሚገባ ገለጸ

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) ዛሬም እንደ ትናንቱ የነበሩብንን ፈተናዎች በድል ተሻግረን እጃችንን ለምስጋና በመዘርጋት ያሉንን ትሩፋቶች ካሉብን ተግዳሮቶች በማስበለጥ መጓዝ እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ገለፁ፡፡

በቀደምት ጊዜያት የታሪክን መልካም ጎን ከማውጣት ይልቅ የነበሩ ተግዳሮቶችና ጥፋቶች ላይ ትኩረት ስናደርግ ቆይተናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህም መልካም እሴቶች ላይ ውሃ የሚቸልስ እንዲሁም የነገን ጉልበት የሚያልም ነው ብለዋል፡፡

ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት ሚኒስትር ዴኤታው ፤ ታድያ የሚታዩ ችግሮችን ብቻ ሳይሆን የተሰሩ ጀብዶችን መንጥሮ በማውጣት መመሰጋገን ለነገ ስንቅ ይሆናል ያሉት ነው ያሉት፡፡

የመመሰጋገን ባህልን በማሳደግ የወደ ፊቷን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማምጣት መስራት ይገባል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የመመሰጋገን ባህላችንን ማዳበርም ያለንን አቅም አውቀን የነገን ጉልበት እንድናሰባስብ እንደሚረዳን በመገንዘብ ኢትዮጵያን በሳንካዎች መካከል አውጥቶ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ላደረገው ፈጣሪ እንዲሁም ሀገር ወዳድ ጀግኖች የምስጋና እጃችንን ልንዘረጋ እንደሚገባ ገልፀዋል::

የመመሰጋገን ባህላችንን ማጎልበትም መልካም እሴቶች በቀዳሚነት ተርታ እንዲሰለፉ እና ጥፋቶች እና ተግዳሮቶች እንዲወገዱ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

በሔብሮን ዋልታው