መንግሥት ግጭቶች እንዳይፈጠሩ አሰራሮችን ዘርግቶ እየሰራ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 30/2014 (ዋልታ) መንግሥት ግጭቶች እንዳይፈጠሩ አሰራሮችን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ መከላከል ላይ በመስራት ግጭቶችን ማክሸፍ ተችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተከሰቱ ችግሮችንም ክትትል በማድረግ እንዳይስፋፋ በማድረግ ረገድ ሰፊ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ግጭት ሲፈጠር ንጹሃን ሰለባ እንዳይሆኑ ጥበቃ በማድረግና የጽጥታ ኃይሉን ዝግጁ በማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ከሚስተዋሉ ግጭቶች በተጨማሪ የተፈጠረው ድርቅ እየፈተነን ቢሆንም ከፈተናዎች በመማር ጥንካሬ እና ጽናትን በመያዝ እየሰራን ነው ሲሉም አክለዋል፡፡