መንግስት ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር ይሰራል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሐምሌ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) መንግስት ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ስምሪት ስምምነት ባልተፈራረመባቸው ሀገራት በህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው ዜጎች እየተሰደዱ እንደሚግኝ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ስምሪት ባልተፈራረመባቸው ወደ ታይላንድ እና ሚያናማር እየሄዱ መሆኑን ተናግረው አሁን ላይ የእነዚህ ሀገራት የውጭ ግንኙነት የሚሽፍኑት የኢትዮጵያ ሚሲዎኖች በህንድ እና ቱርክ ያሉት መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ወደ ታይላንድ እና ሚያናማር ተሰደው በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር የማስመለስ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል።

መንግስት ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር እንደሚሰራና ህብረተሰቡም ከህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩለ 4ኛው የፋይናንስ ልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መከናውኑን ገልጸው የፋይናንስ አቅርቦት ለዘላቂ ልማት አስፈላጊነት ላይ በስፋት ውይይት መደረጉን አንስተዋል።

ኢትዮጵያም የራሷን እና የአፍሪካን ድምጽ በጉባኤው በተገቢው መንገድ አስደምጣለች ብለዋል።

በመስከረም ቸርነት