ሰኔ 26/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህውሃት የሽብር ቡድን ላይ ህግን ለማስከበር የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ እየተወጣ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
ሰራዊቱ በተካሄደው ዘመቻ በሽብር ቡድኑ ንጹሃንን ሽፋን በማድረግ በተከፈተበት ጥቃት ብዙ መስዋትነትን የከፈለ ሲሆን ይህም ለህዝባ ባለው ውግንና ሲል ሰራዊቱ ለሃገር የከፈለው መስዋዕትነት ነው፡፡
የሽብር ቡድኑ እንደለመደው የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን በተለያየ መንገድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስም ለማጥፋት ቢሞክርም ሰራዊቱ አንደኛ ለህግ ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋትነትን መርጧል ፤ የሽብር ቡድኑ ሰራዊቱ ለህዝብ የከፈለውን መስዋትነት እንደሽንፈት ቆጥሮ ለፕሮፓጋንዳ ቢያውለውም የመቀሌና የትግራይ ህዝብ የሰራዊቱን ጨዋነት እና ከአካባው የወጣበት መንገድ ያውቃልና በዚህ የሚታለል አይሆንም።
የኢትዮጵያን ህዝብ ደጀን ያደረገ ሰራዊት ሁሌም አሸናፊ ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡