መደጋገፋችን የቆየ እሴታችን ቢሆንም ይበልጥ በማጎልበት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ሰኔ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) መደጋገፋችን የቆየ እሴታችን ቢሆንም ይበልጥ በማጎልበት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

የ2017 ዓ.ም ክልል አቀፍ የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በኮምቦልቻ ከተማ ተጀምሯል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በየአካባቢያችን የሚገኙ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ እና በተለያዩ በጎ ሥራዎች በመሰማራት የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራትን ማሳለፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሰው እና የተፈጥሮ ግንኙነት የተስማማ ይሆን ዘንድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአረንጓዴ አሻራ ሊሳተፍ ይገባልም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርኃግብር የአረጋዊያንን ቤት በመጠገን፣ በችግኝ ተከላ እና የጎዳና ላይ ሩጫ በማከናወን፣ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት፣ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ በማድረግ እና የደም ልገሳ በማከናወን መካሄዱን አሚኮ ዘግቧል።

በመርኃ ግብሩ ርእሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ከፍተኛ የክልል የሥራ ኃላፊዎቸ ተገኝተዋል።