መጀመሪያው የጉጂ ኦሮሞ ገዳ ጥናትና ምርምር ፎረም እየተካሄደ ነው

ሚያዚያ 15/2013 (ዋልታ) – የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የጉጂ ኦሮሞ ገዳ ጥናትና ምርምር ፎረም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።

ፎረሙን በይፋ የከፈቱት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ የጉጂ ኦሮሞዎች የተለያዩ ባህላዊና ትውፊታዊ ሥርዓቶች ያሏቸው መሆኑን ገልፀው እነዚህን ስርዓቶች በቀጣይነት ለማበልፀግ የጉጂ ፎረም አስተዋፅኦ የላቀ ነው ብለዋል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም የገዳ ባህል ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት አቋቁሞ በ1ኛ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ከ700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በጥናታዊ ጽሑፎቹም የገዳ ሥርዓት በጉጂ ኦሮሞ የማስተዳደር ጥበብ፣ ፍልስፍና ዙሪያ ሲሆን የገዳ ሥርዓት ከሰው ልጆች ሰብዓዊ መብቶች ጀምሮ ብዝሃሕይወትና እንስሳት አያያዝ የተመለከተ ጽሑፍ በመቅረብ ላይ ይገኛል።

የጉጂ አካባቢ በተፈጥሯዊ መስህቦቹ የለመለመ፣ ባህሉና ታሪኩ በብዙዎች የማይታወቅ በመሆኑ ፎረሙ እርሱን ማሻሻልና ማሳደግን አላማ ያደረገ ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ፎረም 19 ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርባሉ ተብሏል።

(በደረሰ አማረ)