ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ የቦርዱ የምርጫ ውጤት ይፋ በመደረጉ ድጋፉን የገለጹ ሲሆን ፣ በምርጫው የተሳተፉ አካላትን ማመስገናቸውን ከህብረቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የህብረቱ ሊቀ መንበር የምርጫ ቦርዱ ይፋ ያደረገውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት ፣ የኮቪድ 19 ሁኔታን ተቋቁሞ የተሳካ ምርጫ ለማድረግ በምርጫው የተሳተፉ አካላት ድርሻ የጎላ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የሚመራው የህብረቱ ታዛቢ ቡድን በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ጳጉሜን 2 የሚካሄደውን ምርጫ የሚታዘብ መሆኑን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል፡፡