ሚኒስቴሩ ለመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ

ታኅሣሥ 10/2014 (ዋልታ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ለመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ  በሆስፒታሉ ከቀዶ ህክምና ጋር ተያይዞ አስፈላጊ የሆኑ ቁሶች ፍላጎት በመኖሩ ለዚሁ ግዥ እንዲውል እንደሚደረግ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ እንደ መንግሥት መስሪያ ቤትም ሆነ ሰራተኞቹ በግል በርካታ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡