ሚኒስቴሩ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የገቢዎች ቢሮ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ጥር 22/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የገቢዎች ቢሮ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው አስታወቁ።
ሚኒስቴሩ ለክልሉ የገቢዎች ቢሮ ካደረገው ድጋፍ መካከል መኪና፣ የጣት አሻራ፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተር፣ ፕሮጀክተር እና ሌሎችም ቁሳቁስ የሚገኙበት ሲሆን ዋጋቸውም 5 ሚሊዮን 608 ሺሕ 94 ብር እንደሆነ ተገልጿል።
የክልሉ የገቢዎች ተቋም በተጠናከረ መንገድ ሥራውን እየሠራ የሕዝብን የመልማት ጥያቄ በአግባቡ እንደሚለስ በቁሳቁስ፣ በአመራር እና በባለሙያ በቀጣይነት እገዛ የሚደረግ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።