ሚኒስቴሩ በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ እየመከረ ነው

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡
ሚኒስትሩ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ከደቡብ ክልል ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የትምህርት ዘርፍ አካላት ጋር ነው እየመከሩ የሚገኙት፡፡
ሚኒስትሩ ከውይይቱ በሻገር በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመርኃ ግብሩ የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡