ሚኒስቴሩ በ10 ዓመቱ የልማት መሪ ዕቅድ ላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እየተወያየ ነው

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ሚያዝያ 09/2013 (ዋልታ) – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ10 ዓመቱ የልማት መሪ ዕቅድ ላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው መሪ ዕቅዱ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራት እንደሚያረጋግጥና በጥናትና ምርምር የማህበረሰቡን ችግር እንደሚፈታ እምነት ተጥሎበታል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ ሀገር በቀል ዕውቀቶች ላይና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት አድርገው ለመስራት መዘጋጀታቸውም በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ውይይቱ ነገም ቀጥሎ ይውላል ነው የተባው፡፡

(በተስፋዬ አባተ)