ሚኒስቴሩ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ ጥሪ አቀረበ

መጋቢት 8/2014 (ዋልታ) ትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ ጥሪ አቀረበ፡፡

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸውን የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ የሚከተሉትን መረጃዎች ተማሪዎች እንደሚለከቱ ጠይቋል፡፡

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የገለፀው ሚኒስቴሩ ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን አሳውቋል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ያሳሰበው ሚኒስቴሩ በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስተናግድ መሆኑንም ገልጿል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW