ሚኒስቴሩ “ኢትዮጵያ ታምርት” በተሰኘ ንቅናቄ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ የሚያደርገውን “ኢትዮጵያ ታምርት” የተሰኘ ንቅናቄ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።

ሚኒስቴሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት ያለመ ኢትዮጵያ ታምርት የሚል ንቅናቄ ይፋ እንደሚያደርግም ነው ያስታወቀው።

ለዚህም ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና አመራሮች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተጋረጡ አደጋዎች ምንድናቸው አደጋ የተጋረጠባቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመታደግ በምን አይነት መንገድ መፍትሔ ይሰጣቸው በሚልም ሚኒስቴሩ ከባለሙያዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ  ሚኒስቴሩ በከፍተኛ አመራሮችን የሚመራና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል።

በዙፋን አምባቸው

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!