ነሐሴ 23/2014 (ዋልታ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ውሃ ኮርፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት በደቡብ ኮሪያ ሲዎል ተፈራረመ።
የደቡብ ኮሪያ ውሃ ኮርፖሬሽን ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓርክ ጄይ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ ባደረጉት ትግግር የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት እንደማንኛውም ሀገር የዲፕሎማሲና የልማት ትብብር ብቻ ሳይሆን በደም የታተመ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከሚኒስቴሩ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከድርጅቱ ጋር በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ በቀጣይነት መሥራት እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸዋል።
የድርጅቱ ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በጥቅምት ወር 2015 ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW