ሚኒስቴሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ጀመረ

ሐምሌ 01/2013 (ዋልታ) – የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ጀምሯል፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር በፌደራል ሚኒስቴር ተቋማት እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም በአዲስ አበባ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ 08 ለሚገኙ ሁለት የአቅመ ደካማ ቤት የማደስ ስራን ተረክቧል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በክረምቱ ወራት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን መርዳት እንደሚገባ ጠቁመው፣ ተቋማቸውም ቤቶቹን የማደስ ተግባር በፍጥነት እንሚያከናውን ገልጸዋል፡፡

በክረምቱ ወራት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን መርዳት እንደሚገባም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህር ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጨምር የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች፤  የሚኒስቴሩ ተጠሪ የከፍተኛ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ማስጀመራቸውም የሚታወስ ነው፡፡

(በሰለሞን በየነ)