ሚኒስቴሩ 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በድሬ ንዑስ ተፋሰስ አካሄደ

 

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በኦሮሚያ ክልል ፊኒፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን በረኸ ወረዳ ቡራ ደብ ደቤ ቀበሌ በድሬ ንዑስ ተፋሰስ ነው 10 ሺሕ ችግኞችን ነው የተከለው።

የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢኒስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሰራተኞች ናቸው በአረንጓዴ አሻራው ተሳታፊ የሆኑት።

አካባባቢው ለአዲስ አበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ ከሚያቀርበው የድሬ ግድብ ተፋሰስ እንደመገኘቱ ቦታውን በአረንጓዴ መሸፈን አስፈላጊ በመሆኑ የችግኝ ተከላውን አካሂደናል ያሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በተደራጀ መንገድ እንክብካቤም ይደረጋል ብለዋል።

ምቹ የከባቢ አየርን ለመፍጠር የደን ሽፋናችንን ለመጨመር የተፈሰስ አካባቢዎችና የውሃማ ቦታዎች በተገቢው መንገድ የውሃ አቅርቦት እንዲኖራቸው ለማድረግ የችግኝ ተከላው ተጠናክሮ መቀጠል እንደ ባህል መያዝ አለበት ተብሏል።

ችግኝ በሚተከልባቸውም አካባቢዎች ያለው መኅበረሰብም በባለቤትነት መንፈስ መከባከብም እንዳለበት ነው የተገለፀው።

በምንይሉ ደስይበለው