ሚኒስትሩ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ሰበሰበ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው በሩብ ዓመቱ 76 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 70 ነጥብ 1 ቢሊዮን መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው አሳውቀዋል፡፡

ገቢው ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የንግድ ማጭበርበር እና በፀጥታ ችግሮች ውስጥ እለች የተገኘ አበረታች ነው መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡