ሚኒስትሩ የአኮቦ የወርቅ ማምረቻን ሥራ አስጀመሩ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ታከለ ኡማ የአኮቦ የወርቅ ማምረቻ ፋበሪካን ሥራ በጋምቤላ ከተማ ተገኝተው አስጀምረዋል፡፡
በአኮቦ የወርቅ ማምረቻ ሥራ ማስጀመሪያ ስነ ሥርዓት ላይ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ወርቅ ማምረቻ ፋበሪካው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅና በዓመት ከ2 ሺሕ ኪ.ግ በላይ ወርቅን የሚያመርት መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጹት፡፡
ፋብሪካው በዓመት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የማስገኘት አቅም ያለው፣ ለኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ትልቅ ፋይዳ የሚኖረውና የሀገቱን ማእድናት በሰፊው ጥቅም ላይ እንዲውሉ የምናደርገው ጥረትን የሚደግፍ ይሆናል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡