ማህበረሰቡ አንድነቱን በማጠናከር የውጭ ጫናን መመከት እንዳለበት ተጠቆመ

ግንቦት 21/2013 (ዋልታ) – ማህበረሰቡ አንድነቱን በማጠናከር የውጭ ጫናን መመከት እንዳለበት የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን አሳሰቡ፡፡

የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለቀጣይ አምስት ዓመታት ያስተዳድሩኛል ያላቸውን አመራሮችና የምክር ቤት አባላት መርጧል፡፡

በዚህም 38 ለውድድር ከቀረቡ እጩዎች 14ቱን የመረጠው ማህበሩ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍንን ፕሬዝዳንት አድርጎ ሲሾም አቶ ዘውዱ አምደ ሚካኤልን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጓል፡፡

የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ማህበሩ ከዚህ በፊት የነበሩበትን ችግሮች በመቅረፍ ለሃገር አሻራ የሚሆኑና ትውልድ የሚዘክራቸውን ስራዎች መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

(በዙፋን አምባቸው)