ማህበሩ በሁለቱ ክልል ለተከሰተው የድርቅ አደጋ 206 ሚሊዮን ብር እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

የካቲት 21/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ለተከሰተው የድርቅ አደጋ 206 ሚሊዮን ብር እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ማህበሩ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የገንዘብን ጨምሮ የምግብ እህል እርዳታ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሐፊ ጌታቸው ታዓ በ9400 የኤስኤም ኤስ መልዕክትን ጨምሮ ቢሮው ድረስ በመገኘት በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ማህበሩ የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ 5 ሺሕ 200 አባዎራዎች እርዳታ እንደሚያደርግም ነው ያስታወቀው።

በሱራፌል መንግስቴ