ምርቱን አቋርጦ የነበረው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ሥራ ጀመረ

የካቲት 9/2014 (ዋልታ) በነዳጅ አቅርቦት ችግር ለአንድ ሳምንት ማምረት አቋርጦ የነበረው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ምርት መጀመሩን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ነዳጅ ጫኝ መኪና አሽከርካሪዎች ለደኅንነታቸው በመስጋት ወደ አካባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከየካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ማምረት አቁሞ እንደነበር አስታውቋል፡፡

ሆኖም ከየካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ አቅርቦት ችግሩ በመስተካከሉ ወደ መደበኛ የማምረት ሥራው መመለሱ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዓመት 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ስኳርና 20 ሚሊየን ሊትር ኢታኖል የማምረት አቅም ያለው ስኳር ፋብሪካው በ1991 ዓ.ም ማምረት ሲጀምር የነበረው 6 ሺሕ 476 ሄክታር መሬት አሁን ላይ 21 ሺሕ ሄክታር መድረሱ ታውቋል።