መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የበጋ መስኖ ስንዴ ምርትን በማሰባሰብ የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር እና አላስፈላጊ የሆኑ የግብይት ሰንሰለትን በማሳጠር ምቹ የሆነ የገበያ ትሥሥር መፍጠር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱ የክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን፣ የግብርና እና ንግድ ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
የገበያ ትስስር ለመፍጠር ማነቆ የሚሆኑ አሰራሮችንና የገንዘብ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራም ተነግሯል።
የበጋ መስኖ ስንዴ ምርትን በመሰብሰና ለገበያ በማቅረቡ ረገድ የኅብረት ሥራ ዩኒየኖች ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሚሰራም በውይይት መድረኩ ተመላክቷል።
በሳራ ስዩም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!