ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢገጥመን ሀገራዊ የብልጽግና ሕልማችን ሳይደናቀፍ ይቀጥላል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሚያዚያ 09/2013 (ዋልታ) – ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢገጥመን፣ ሀገራዊ የብልጽግና ሕልማችን ሳይደናቀፍ ይቀጥላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዐውደ ርዕይን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፤ በዚህም ኢመደኤ በመላው ሀገሪቱ ያሉ ተቋማት ተምሳሌትነቱን ሊከተሉ የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

ከመሠረተ ልማት በተጨማሪ፣ የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት መሪ አፍሪካዊ የሳይበር ተቋምን እውን የማድረግ ራእይን የያዘ ነው ሲሉ ነው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው የገለጹት።

የዛሬ ዐሥር ዓመት የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ተወጥኖ መጀመሩን ጠቅሰው ከብዙ የሥራ መዘግየትና መጓተት በኋላ፣ የዛሬ ሦስት ዓመት ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት ታልሞ ሥራው መቀጠሉን አስታውሰዋል፡፡