የካቲት 14/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችን የሚሾሙበትን ልዩ ስብሰባ እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ከዚህ በፊት የ42 ዕጩዎችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በዚህም ምክር ቤቱ የተገኘውን ግብዓት ከተመለከተ በኋላ መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙለት ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1. መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)
2. ሂሩት ገብረሥላሴ
3. ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር)
4. አምባሳደር አይሮሪት መሃመድ (ዶ/ር)
5. ብሌን ገብረመድኅን
6. ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)
7. ዘገየ አስፋው
8. መላኩ ወልደማሪያም
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
10. ሙሉጌታ አጎ እና
11. አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ዕጩ ኮሚሽነር ሆነው ቀርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡