ምክር ቤቱ 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ያካሂዳል

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔው ነገ ያካሂዳል፡፡
ምክር ቤቱ በነገ ውሎው የ10ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ ያጸድቃል ተብሏል፡፡
በመቀጠል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የ2ዐ14 በጀት ዓመት የ10 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የሚኒስቴሩ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅን ለመደንገግ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ነው ያመላከተው፡፡