ም/ቤቱ ስልጠና እየሰጠ ነው

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለስድስተኛው የፖርላማ ዘመን ለምክር ቤቱ አባላት ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናው በምክር ቤቱ ህገመንግስታዊ ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።
በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ የምክር ቤቱ አባላት የህገ መንግሥት የበላይነት እንዲረጋገጥና ህብረ ብሔራዊነትን ለማጠናከር ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
አባላቱ በአገሪቱ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ሊሰሩ እንደሚገባም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ የተከናወኑ መልካም ተግባራትን ማስቀጠል እና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አፈ ጉባኤው አብራርተዋል።