ም/ቤቱ የአሚኮ የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ።

ለሚዲያው የቦርድ ሰብሳቢና አባላት ሹመት በክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ደ/ር) የቀረበ ሲሆን ምክር ቤቱም እጩዎችን ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፡-
1. ግሮማ የሺጥላ ሰብሳቢ
2. አህመዲን አሕመድ (ዶ/ር) አባል
3. ጥላሁን መሃሪ (ዶ/ር) አባል
4. ግዛቸው ሙሉነህ አባል
5. አለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር) አባል
6. ዳዊት መኮንን (ዶ/ር) አባል
7. እንግዳወርቅ ታደሰ አባል
8. ተስፋሁን ይስማው አባል
9. ሙሉቀን ሰጥዬ የቦርድ አባላትሆነው በአምስት ተቃውሞ በሰባት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ተሹመዋል።

ለአሚኮ ሥራ እስፈፃሚነት ከዚህ በፊት ከሪፖርተርነት ጀምሮ በተለያዩ ኃለፊነት ያገለገሉትና አሁንም የአሚኮ ሥራ አስፈፃሚ ሆነው የሚያገለግሉት የነበሩት ሙሉቀን ሰጥዬ በምክር ቤቱ በ2 ተቃውሞ በ3 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የአሚኮ ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።

ምንይሉ ደስይበለው (ከባሕር ዳር)