ም/ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የሚመክር ይሆናል፡-

  1. የም/ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣
  2. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ም/ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች ኮሚሽነሮች አቅራቢ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ሹመቱን ማጽደቅ፣
  3. የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 251/1993ን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣
  4. የፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤትን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 556/2000 ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠብቃል፡፡