ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጃንሜዳ ታቦት ማደሪያን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስረከቡ

ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጃንሜዳ ታቦት ማደሪያን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስረክበዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን የተለያዩ ሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጃንሜዳ የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል ።

ጃንሜዳ ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ከምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ትብብር በቤተክርስቲያኗ እና በህዝበ ክርስቲያኒቱ ስም አቡነ ማቲያስ ምስጋና አቅርበዋል ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው  የጥምቀት በአል የሃገርን ባህል ከማስተዋወቅና ገፅታን ከመገንባት አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ ይህን ሃማኖታዊ በአል ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በአል ምቹ እንዲሆን ላደረገው ጥረት አመስግናለች፡፡

(በሄብሮን ዋልታው)