ም/ጠ/ሚኒስትሩ በጎንደር በተፈጸመው ህገወጥ ድርጊት ማዘናቸውን ገለጹ

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጎንደር በተፈጸመው ህገወጥ ድርጊትና በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገለጹ።
“ከኢድ እስከ ኢድ” ወደ ሀገር ቤት መርኃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ሲሆን በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያዊያን ለዓለም ልናሳያቸው የምንችለው እልፍ እሴት እና በጎነት አሉን ብለዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚስተዋሉ ችግሮች ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ ብሎም ትውፊታዊ መሠረት የሌለውና ኢትዮጵያዊያንን የማይወክል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በትላንትናው እለት በጎንደር ከተማ በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልፀው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ዲያስፖራው ሀገሩን የሚያለማ ሀገሩን የሚወድ መሆኑን ገልፀው ወደ ሀገር ቤት ለገቡ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሃኒ አበበ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!